Posted by admin on 2026-06-30 11:46:48 | Last Updated by admin on 2026-07-10 23:35:22
Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin | Telegram | Visits: 20
ኩፍኝ በMeasles virus የሚከሰት፣ በጣም ተላላፊ የቫይረስ በሽታ ነው። በተለይ ከ5 ዓመት በታች ባሉ ሕፃናት ላይ ከባድ ሕመምና ሞት ሊያስከትል ይችላል።
በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ
ከነሐሴ 2013 ዓ.ም እስከ ታኅሣሥ 2017 ዓ.ም ድረስ በመላ ሀገሪቱ 78,106 የኩፍኝ ታካሚዎች እና 633 ሞቶች ተመዝግበዋል
ማንን በብዛት ይጎዳል?
ኩፍኝ በሁሉም ዕድሜ በተለይ፦
ከ5 ዓመት በታች ያሉ ሕፃናት፣ ያልተከተቡ ሕፃናት፣ በHIV የተያዙ ሕፃናት፣ የምግብ እጥረት (Malnutrition) ያለባቸው፣ የበሽታ መከላከያ አቅማቸው የቀነሰ ሕፃናት
እንዴት ይተላለፋል?
ኩፍኝ በአየር በሚበተኑ ትንፋሽ ጠብታዎች በቀላሉ ይተላለፋል። በሳል፣ በማስነጠስ ወይም በቅርብ ግንኙነት ይሰራጫል
⏳ የመታቀፍ ጊዜ (Incubation Period)
ምልክቶች ከ7–21 ቀናት (በአብዛኛው 10–14 ቀናት) ውስጥ ይታያሉ። ታካሚው ሽፍታው ከመውጣቱ 4 ቀናት በፊት እስከ 4 ቀናት በኋላ ድረስ በጣም ተላላፊ ነው
⚠️ ምልክቶች
ከፍተኛ ትኩሳት
ሳል
ንፍጥ
የዓይን መቅላት
በአፍ ውስጥ ነጭ ነጥቦች (Koplik spots)
ከፊት ጀምሮ ወደ መላው ሰውነት የሚሰራጭ የቆዳ ሽፍታ
⚠️ ውስብስቦች
የሳንባ ምች፣ የጆሮ ኢንፌክሽን፣ ተቅማጥና ድርቀት፣ የአንጎል ኢንፌክሽን (Encephalitis)፣ ዓይነ ስውርነት፣ ሞት
እንዴት እንከላከል?
✅ ልጆቻችንን በወቅቱ ማስከተብ
በ9 ወር
በ15 ወር (1 ዓመት ከ3 ወር)
✅ የታመመ ልጅን ለብቻው ማቆየት
✍መልእክት
ኩፍኝ በክትባት ሙሉ በሙሉ ሊከላከል የሚችል በሽታ ነው። ልጆቻችንን በወቅቱ በማስከተብ ሕይወታቸውን እንጠብቅ!