የአናቶሚካል ስካን (Anatomical Scan) ምንድን ነው?

እናቶች እና ህጻናት Education

Posted by admin on 2026-05-20 09:09:57 | Last Updated by admin on 2026-07-11 01:01:34

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin | Telegram | Visits: 59


የአናቶሚካል ስካን (Anatomical Scan) ምንድን ነው?

✅ብዙውን ጊዜ በሁለተኛው የእርግዝና አጋማሽ (ከ18-22 ሳምንታት ባለው ጊዜ) የሚደረግ አልትራሳውንድ ሲሆን፣ የፅንሱን እድገትና ጤንነት በዝርዝር ለመመርመር የሚረዳ ወሳኝ ምርመራ ነው።

✅ምርመራው በዋናነት ምን ምን ነገሮችን ይመለከታል?

1.የፅንሱን የአካል ክፍሎች፦ የጭንቅላት፣ የልብ፣ የኩላሊት፣ የሆድ እቃ እና የአከርካሪ አጥንት እድገት ትክክለኛ መሆኑን ያረጋግጣል።
2• የፅንሱን የክብደት መጠን፦ ፅንሱ ካለበት የርግዝና ሳምንት ጋር የሚመጣጠን እድገት እያሳየ መሆኑን ይለካል።
3• የእንግደይ ልጅ (Placenta) ሁኔታ፦ የእንግደይ ልጅ ያለበትን ቦታ እና ከማህፀን በር ያለውን ርቀት ይመረምራል
4• የሽርት ውሃ መጠን፦ በፅንሱ ዙሪያ ያለው የፈሳሽ መጠን በቂ መሆኑን ለማረጋገጥ ይጠቅማል።

?ይህ ምርመራ ለምን አስፈለገ?
ይህ ምርመራ አብዛኛውን ጊዜ "Anomaly Scan" ተብሎም ይጠራል፤ ምክንያቱም ማንኛውንም አይነት መታከም የሚችሉ የአካል ጉድለቶችን ቀድሞ ለመለየትና አስፈላጊውን ዝግጅት ለማድረግ ስለሚረዳ ነው።

?ማሳሰቢያ፦ ይህ ምርመራ የልጁን ጾታ ለማወቅ ብቻ ሳይሆን፣ ከዛ በላይ ለፅንሱ ጤንነት ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።

ቀጠሮ ለማስያዝ እና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ይደውሉልን፡፡
? +251940363738/ +251935878781
አድራሻ ፡ አ.አ ፣ 6 ኪሎ አካባቢ ከየካቲት 12 ሆስፒታል ጀርባ ወደ ናዝሬት ት/ቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ

ET(Ethiopia) Care MCH Center ኢት(ኢትዮጵያ) ኬር የእናቶችና ህፃናት ህክምና ማዕከል
@etcaremchcenter @mchcenter